በመረጃው
መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ሑመራ ከተማ ውስጥ ሰፍረው የሚገኙት የኢህአዴግ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የተሰማሩበትን ስራ
ወደ ጎን በመተው። ጨለማን ተገን በማድረግ በሴቶች ላይ ዓመፅ ማካሄድ፤ የህዝብ ንብረት መስረቅና ማበሳበስ የተለመደ ስራ አድርገው
እየተጠቀሙበት መሆኑን የገለፀው መረጃው በተለይም ዲማ በተባለው ቦታ የሚገኙት ኮማንዶ በመባል የሚታወቁት ወታደሮች አዛዥ የሆነው
መቶ አለቃ ታፈሰ የተባለው ወታደር ሃይማኖት የተባለችውን ወጣት በሽጉጥ አስፈራርቶ ክብረ ንፅህናዋን እንደደፈራት የተገኘው መረጃ
አስታውቋል።
በተጨማሪም በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙት የኮማንደዋ አባላት ፀጋይ፤
ዳንኤልና አንድ ለግዜው ስሙ ያልታወቀ ወታደር ሶስቱም አንድ ላይ በመሆን ወደ ከተማዋ በመሄድ ይበልጣል የተባለውን የሆቴል ባለቤት
የጠየቁትን ስላላሟላላቸው ብቻ የሰከሩ መስለው በዱላና በጠርሙስ ደብድበው በሆቴሉ ደጃፍ ላይ ጥለውት እንዳመለጡ መረጃው አክሎ አስረድቷል።