Wednesday, July 15, 2015

የመቐለ ከተማና የአካባቢው ህዝብ ፍትሃዊ ባልሆነ የግብር አከፋፈል ምክንያት ብሶቱን እያሰማ መሆኑን ምንጮቻችን ከከተማው አስታወቁ።



    የመቐለ ከተማና የአካባቢው ህዝብ ፍትሃዊ ባልሆነ የግብር አከፋፈል ምክንያት ብሶቱን እየገለፀ መሆኑን የገለፀው መረጃው ከሐምሌ 1/2007 ዓ/ም ጀምሮ በየደረጃው እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል መንግስት እየተጠቀመው ያለው የግብር አከፋፈል ግምታዊ እንጂ ሳይንሳዊ አይደለም፤ አንድ ዓይነት ካፒታል ያላቸው ነጋዴዎች የተለያየ ግብር እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው፤ በጥናት ባልተደገፈ የግብር አከፋፈል ህዝቡ እየተሰቃየ ነው፤ ለምን ይህን ይሆናል ብለን ብንጠይቅም ቆይተን እናጠናዋለን ስለሚሉን ሳንወድ ተበድረንም ቢሆን እየከፈልን ነው፣ የሚያበድራቸው ያጡት ደግሞ ወደ ሚመለከታቸው አካላት እየሄዱ የንግድ ፈቃዳችን ተረከቡን እያሉ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
    አንከፍልም ብለው የንግድ ፈቃዳቸው ካስረከቡ ነጋዴዎች መሃል ወ/ሮ አስቴር ረዳ የሮማናት ቁርስ ቤት ባለቤት፤ አቶ መዓሾ ሊላይ የማስተር ኤሌክትሮኒክስ ባለቤት፤ ወ/ሮ ፋጡማ ኑሩህሴን የላውንድሪ ባለቤት የሚገኙባቸው እንደሆኑ መረጃው አክሎ አስረድቷል።