Wednesday, July 15, 2015

በኦሮሚያ ክልል፤ ሰሜን ሽዋ ዞን የሚገኙ የመድረክ ተቃዋሚ ድርጅት አባላት በስርዓቱ ካድሬዎች ግፍ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



    በኦሮሚያ ክልል፤ ሰሜን ሽዋ ዞን፤ የሸኖ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ጉታ ያዴታ የተባለ የመድረክ ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሰኔ 21/2007 ዓ/ም ከሰንዳፋ ወደ ሸኖ እየሄደ በነበረበት ሰዓት መንገድ ላይ ጠብቀው በዱላ ጭንቅላቱ በመምታት ገድለነዋል ብለው ጥለውት መሄዳቸውን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
    መረጃው በማከል በከባድ ድብደባ የተጎዳውን ወገን መንገድ ላይ ተጥሎ ያዩትን የአካባው ህብረተሰብ ወደ ፖሊስ አስታውቀው እንዲነሳ ካደረጉት በኋላ የደበደቡኝ ሦስት የስርዓቱ ካድሬዎች ናቸው፤ አስቀድመውም የመድረክ አባል በመሆኔ በተደጋጋሚ እያስፈራሩኝ ቆይተዋል በማለት ቃሉን እንደሰጠ የአይን እማኞች መናገራቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።