Monday, August 24, 2015

በቡሬ ግንባር የሚገኙ የ25ኛ ክፍለ ጦር ወታደሮች በክፍሉ ውስጥ በተመደቡ ሴት ወታደሮች ምክንያት ራስ በርሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸው ታወቀ።



     በቡሬ ግንባር የሚገኙት የ25 ክፍለጦር የስርዓቱ ወታደሮች በክፍላቸው በተመደቡ ሴት ወታደሮች ምክንያት ራስ በራሳቸው እየተገዳደሉ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው በዚህ መሰረትም ሓምሌ 26/ 2007 ዓ/ም ዳርጋው የተባለ ወታደር በሴት ወታደሮቹ ምክንያት 5 ወታደሮች ገድሎ ለራሱም ህይወቱን ማጥፋቱ ተገለጸ።
    የተገደሉትን ወታደሮች ስም አምሳ አለቃ ደምሴ፤ አስራአለቃ ሁሴን፤ አስራ አለቃ ጀማል፤ ምክትል አስራ አለቃ ገብረመድህን ( ወዲ ምጉላትና) አሸናፊ የተባለ ወታደር የሚገኙባቸው እንደሆኑና ወደ ጥበቃ እየወጡ በነበሩበት ሰዓት እንደገደላቸው ለማወቅ ተችሏል።