በምንጮቻችን
መረጃ መሰረት ድሆች ተማሪዎችን ለማገዝ በሚል የዓለም ባንክ ድርጅት ባወጣው ፕሮግራም መሰረት ለአንድ ችግረኛ ተማሪ በከፍተኛ ት/ቤት
ገብቶ በእንጅነሪንግና ኮንስትራክሽን ትምህርት ለመከታተል የሚያስችለው ለአራት ዓመት 70 ሺ ብር ሂሳብ እየተከፈለው ለመማር የተያዘው
ፕሮግራም በውክልና ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መስጠቱና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ስምምነት መፈጸሙ
ታወቀ።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ጅማ፤ ባህርዳር፤ አዳማ፤ ሃዋሳ፤ አዲስ አበባና
መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች በውክልና እንዲሰጡ ቢያደረግም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች ግን የህወሃት አባላት ለሆኑት ብቻ እንዲማሩ
እድል በመስጠታቸው ሌሎች ድሃ መሆናቸው የታወቁና ህጋዊ ማረጋገጫ ይዘው የቀረቡትን ግን ቦታ ሞልቷል ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን
ተገልጿል።
ብዛት ያላቸው ወጣቶች የስርዓቱን የተሳሳተ አሰራር በመቃወም ወደ ህወሓት
ጽሕፈት ቤት በመሄድ ህጋዊነት ያልተከተለ አሰራር ለምን ይፈፀማል? ለድሆች ተብሎ ከአለም ባንክ የመጣውን የትምህርት እድል ለምን
አግባብ ባለው መንገድ እንዲፈፀም አልተደረገም? ብለው በጠየቁበት ግዜ የሚመለከታቸው የጽሕፈት ቤቱ አካላት የምናውቀው ነገር የለም
ብለው እንደመለሷቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።