ሓምሌ
26 /2007 ዓ/ም ስርአቱ በጠራው ስብሰባ ላይ እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች እንደተገኙ የገለጸው
መረጃው የስብሰባው አጀንዳም በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በክረምት ወቅት በፍላጎታቸው ነፃ አገልግሎት
እንዲሰጡ የሚል እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በማስከተል ተማሪዎቹ ባለፈው አመታት በፍላጎታቸው በክረምት ወራት
የነፃ አገልግሎት እየሰጡ መቆየታቸው የሚታወቅ ሁኖ። በአሁኑ ዓመት ግን አብዛኛው በነፃ ያገለገለውን ተማሪ ትታችሁ በቅድሚያ የህወሃት
አባላት የሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ስራ እየተሰማሩ እንደሆኑ በማየታችን ነው ወደ ስብሰባው ያልመጣነው ብለው መናገራቸውን የደረሰን
መረጃ አብራርቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ተማሪዎቹ በአንድ አገር ሁለት ዓይነት ዜጋ መኖሩን
አውቀናል፤ እባካችሁ ከቤተሰቦቻችን ጋር ክረምቱን እንድናሳለፍ አድርጉን? በኋላ እንደማንኛውም ሰው ራሳችን ስራ መፈለግ ይሻለናል
በማለት በስብሰባው ላይ መሳተፉን አንዳልመረጡ መረጃው አክሎ አስረድቷል።