Tuesday, August 18, 2015

በቤንቺ ማጂ ዞን የሚገኙ አርሶ-አደሮች ለበርካታ አመታት ቡና በመትከል እየተጠቀሙበት የነበረውን መሬት በአስተዳዳሪዎች እየተነጠቁ መሆናቸው ተገለፀ።



    በደቡብ ክልል ህዝቦች፤ ቤንቺ ማጂ ዞን፤ ቤንቺ ሰሜን ወረዳ ጎሊ በተባለው ቀበሌ የሚገኙ አርሶ-አደሮች ለበርካታ አመታት ቋሚ ተክል፤ ቡናና ሌሎች የእርሻ   ውጤቶን በማፍራት ሲጠቀሙበት የቆዩትን ህጋዊ መሬታቸውን የዞኑ አስተዳዳሪዎች መሬቱን ለዲያስፖራ ኢንቨስተሮች በመስጠታቸው ከአካባቢያቸውና ከእርሻ መሬታቸው አስገድደው እያፈናቀሏቸው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ዛሬ ይሁን ነገ መሬታችንን ትተን አንሄድም ያሉትን አርሶ-አደሮች ታጣቂዎችን በማሰማራት አስረው ቋሚ ተክሎቻቸውን በዶዞር እያወደሙት እንደሆኑ ታውቋል።
   ይህ ያለህጋዊ መንገድ የአርሶ-አደሮችን መሬት የመንጠቅ እርምጃ ከሰኔ ወር 2007 ዓ/ም የጀመረ ቢሆንም በተለይ በአሁኑ ሰዓት ግን  በአዋሳኝ መንገድ የሚገኙትን የእርሻ ቦታዎች የዞኑ አስተዳዳሪዎች ከፖሊሶች ጋር በአንድነት በመሆን የእርሻ መሬቱን የመንጠቅ ተግባር በተጠናከረ መልኩ እየቀጠሉበት በመሆኑ በርካታ ዜጎች ለከፍተኛ ማህበራዊ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከአካባቢው ጨምረው አስታውቀዋል።