Sunday, August 30, 2015

በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የክልሉ ተወላጆችና ሃበሽ በሚል የሚጠሯቸው የሌላ ክልል ተወላጆች መካከል በሚከሰት አለመግባባት በየዕለቱ የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልፀዋል።



    እንደምንጮቻችን ገለፃ መሰረት በጂግጂጋ ከተማ ሃበሽ በሚል መጠሪያ በሚጠሩት የሌላ ክልል ተወላጅና በሶማሌ ክልል ተወላጆች መካከል ገዥው የኢህአዴግ መንግስት እየፈጠረው ባለው የማጋጨት ተግባር ምክንያት በየግዜው የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን የገለፀው ዘገባው በከተማዋ በሚገኙት በሁሉም ቀበሌዎች የሚኖሩ የሌላ  ክልል ተወላጆችን እንደሁለተኛ ዜጋ በመቁጠር የሚያንገላቱ ቢሆንም  በተለይ በቀበሌ 04 ቀበሌ 05ና ቀበሌ 06 ላይ ጎልቶ እንደሚታይ ገልፀዋል።
 ይህንን እኩይ ተግባር በማባባስ ከፍተኛውን ሚና ከሚጫወቱት የመንግስት ቅጥረኞች መካከል በየፍተሻ ኬላዎችና በከተሞች የተመደቡት የትራፊክና ተራ የፖሊስ አባላት ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ጂግጂጋ የሚጓዙ የሌላ ክልል ተወላጆችን  በግልፅ ገንዘባቸውንና ንብረታቸውን እንደሚዘርፏቸው ምንጮቻችን አክለው ተናግረዋል።