Tuesday, August 18, 2015

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች ከገቢያችን ጋር የማይገናኝ ከፍተኛ ግብር ተጣለብን በማለት የንግድ ፈቃዳቸውን እየመለሱ መሆኑ ተገለፀ።



    ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች በከተማችን ከገቢያችን ጋር የማይመጣጠን በእጥፍ የጨመረ ግብር እንድንከፍል እየተገደድንን ነው በማለት በርካታዎች የንግድ ፈቃዳቸውን እየመለሱ ይተዳደሩበት የነበረውን ስራ የሰረዙ ሲሆን የግብር አጣጣሉን በተመለከተ ነጋዴዎች ሲናገሩም በገዥው መንግስት ላይ ያላቸው አመለካከት እየታየ የተጣለ መሆኑን አስረድተዋል።
   መረጃው ጨምሮም የንግድና የስራ ፈቃዳቸውን ከመለሱ በርካታ ነጋዴዎችና ባለ ድርጅቶች  መካከል ባለፈው ዓመት 52 ሺህ ብር ግብር የከፈለውና በዚህ አመት 160 ሺህ ብር የተጣለበት በቀድሞው ጤና ጣቢያ አካባቢ የሚገኘው የጋራዥ ባለቤት ሲሆን እስካሁን እየተቋረጠ መፍትሄ ያላገኘውን የመብራት ችግር ግምት ውስጥ ያላስገባና ሚዛናዊ ያልሆነ የግብር አጣጣል በመቃወም የስራ ፈቃዱን መልሷል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ  በፍኖተሰላም ከተማ የመብራትና የመጠጥ ውሃ መቆራረጥ ያጋጠመ ሲሆን በጂጋና ማንኩሳ ከተሞች ለወራት የዘለቀ የስኳር እጥረት ማጋጠሙን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል።