በደቡብ ህዝቦች ክልል ፤ ቤንቺ ማጂ ዞን፤ ሰሜን ቤንች ወረዳ ውስጥ የሚገኙ አርሶ-አደሮች ከፍላጎታቸው ውጭ
ማዳበሪያ እንዲገዙ በስርዓቱ ካድሬዎች እየተገደዱ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ማዳበሪያው ከአካባቢው መሬት ስለማይስማማ አንፈልግም
ቢሉም በስርዓቱ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ጫና እንዲወስዱ መደረጉና ከአቅማቸው በላይ በሆነ መንገድ የወሰዱትን የማዳበሪያ ዋጋ ለመክፈልም
ከብቶቻቸውን እየሸጡ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በወረዳው ውስጥ የሚገኙ አርሶ-አደሮች ቀደም ብለው
የስርዓቱ ካድሬዎች ማዳበርያውን ውሰዱ እያሉ እንዳስጨንቋቸውና በግዜው ያልከፈሉትም በክልሉ በሚገኝ "ኦሞ" በሚል መጠሪያ ከሚታወቀው የድርጅቱ ማይክሮ ፋይናንስ
በብድር እንደወሰዱ አስመስለው ወደ ፍርድ ቤት በማቅረብ ከብቶቻቸውን ሸጠው እንዲከፍሉ እያስገደዷቸው እንደሆኑና ይህን ለመፈጸም
ፈቃደኛ ያልሆኑትን ደግሞ መሬታቸው በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ እንዲያዝ በማድረጋቸው እርሶ-አደሮቹ በስርዓቱ ላይ ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።