Sunday, August 30, 2015

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ማግኘት የሚገባንን ጥቅማጥቅም አላገኘንም በማለት ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት እየለቀቁ መሆናቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረዱ።



    በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከመንግስት ማግኘት የሚገባቸውን የትምህርት እድል የደመወዝ ጭማሪና የተሻሻለ የውሎ አበል ማግኘት ባለመቻለቸው ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት እየለቀቁ ወደ ግል ድርጅቶች እየተቀጠሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በብዛት ከለቀቁ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች መካከል የወረዳው የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅህፈት ቤትና የግብርናና ገጠር ልማት ፅህፈት ቤት ሰራተኞች መሆናቸውን አስረድቷል።
     በመጨረሻም የመስሪያ ቤት ሰራተኞች በውጤት ተኮር አፈፃጸሙ መሰረት ትክክለኛ ማግኘት የሚገባንን ጥቅማጥቅም አላገኘንም በሚል በአካባቢው በሚገኙ የግል ድርጅቶችና ተቋማት የገቡ ሲሆን በብዛት ከተሰማሩባቸው ድርጅቶች መካከልም  የኩል ውሃ ፋብሪካ ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ማከፋፈያ መርከብ የማህበራቶች ዩኒየን በተሰኙትና በመሳሰሉት መሰማራታቸውን ለማወቅ ተችሏል።