የደረሰን መረጃ እንዳመለከተው በሰሜን ጎንደር ዞን ከዚህ በፊት ለበርካታ
አመታት የቅማንት የማንነት ጥያቄ ሲጠየቅ በስራ አስፈፃሚነት ሲነቀሳቀሱ ከነበሩት ኮሚቴዎች መካከል በስውር አንዳንድ ኮሚቴዎች እየታሰሩ
መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በቅርቡ ለቅማንት ወረዳ ከተወሰኑት ቀበሌዎች በተጨማሪ ሌሎችም ወደ ወረዳው መካከል ያለባቸው 2 ቀበሌዎች
አሉ መባሉን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ብጥብጥ ሳቢያ መሆኑን አስረድቷል።
ከዚህ ዞን ሳንወጣ በመተማ ወረዳ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የተከሰተውን ድርቅ
ተከትሎ ፈጥኖ ደራሽ ሰብሎችን ለመዝራት የተሻሻሉ ዝርያዎች እንዲመጣላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው ምንም አይነት ምላሽ ሊያገኙ
አለመቻላቸውን በምሬት ገልፀዋል።