Monday, August 31, 2015

በአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ በግል ባለሃብቶችና በአርሶ አደሮች መካከል የተቀሰቀውን ችግር ለመፍታት ከዞን ተወጣጥቶ የሄደው ቡድን እልባት ሊሰጥ አለመቻሉን አርሶ አደሮቹ ተናገሩ።



   በአንከሻ ወረዳ አየሁ በተባለው ቀበሌ በሚገኘው ሰፊ የእርሻ መሬት የተነሳ ሼክ አላህ ሙዲንን ጨምሮ በግል ባለሃብቶችና በአካባቢው አርሶ አደሮች መካከል የነገሰውን ከፍተኛ ውጥረት ለማርገብ የሚመለከታቸው የአዊ ዞን ከፍተኛ አመራሮችን የያዘው የክልሉ የኢንቨስትመንት ቢሮ ባለሙያ ወደ ስፍራው አቅንተው ያለምንም መፍትሄ መመለሳቸውን የገለፀው መረጃው የችግሩ መንስኤ ገዥው የኢህአዴግ መንግስት በመሆኑ ማንም ሊያደራድረን አይችልም በማለት በእምቢታ መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ከከሳ እስከ አየሁ የተሰራው ጥራት የጎደለው የመኪና መንገድና በየእለቱ የሚቆራረጠው የመብራት ችግር ቋሚ መሆን ግጭቱ እልባት እንዳያገኝ ጫና ማድረጉን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል።