Saturday, August 22, 2015

በረከት አካባቢ ወደ ሚገኘው የኢትዮጵያ ግዛት የሱዳን እርሶ አደሮች በአገሪቱ ወታደሮች እየታገዙ ኢትዮጵያውያን የዘሩትን ማሳ እየገለበጡ በማረስ ላይ እደሚገኙ ተገለፀ።



    በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን፤ ቃፍታ ሑመራ ወረዳ፤ በረከትና አካባቢው የሚገኘው በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የታረሰውና በዘር የተሸፈነው ሰፊ የእርሻ ቦታ የሱዳን አርሶ አደሮች በወታደሮቻቸው ታግዘው የኢትዮጵያን ግዛት ጥሰው በመግባት      አካባቢውን በመቆጣጠር የተዘራውን አዝርእት ገልብጠው ማረሳቸውን ታወቀ።
    ይህ በንዲህ እንዳለ በሱዳን ወታደሮችና በኢህአዴግ ስርዓት ምልሻ ታጣቂዎች መሃከል ነሃሴ 4/2007 ዓ/ም ዓላው በተባለው ቦታ ላይ የተደረገው ውጊያ በአካባቢው ነዋሪ ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ መንገላታት እንደፈጠረ ከቦታው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።