Saturday, August 22, 2015

ለ24ኛ ክፍለጦር ሰራዊት ስታገለግል የነበረችው ወታደራዊ የውሃ ማመላለሻ ቦቴ በመገልበጧ ምክንያት በውስጧ የነበሩት የስርዓቱ ወታደሮች ሙትና ቁስለኞች መሆናቸው ተገለፀ።



    እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት በአውደ ራፊዕና አካባቢው ለሚገኙት ለ24 ክፍለጦር ሰራዊት ስታገለግል የቆየች አንድ የውሃ ቦቴ በመገልበጧ ተሳፍረው ከነበሩት ውስት 6 ወታደሮች ሲሞቱ የመኪናዋ ሾፌር ጨምሮ በርካታ ወታደሮች ደግሞ በከባድ መቁሰላቸውን ታወቀ።
    ከሞቱት ወታደሮች የተወሰኑት ለመጥቀስ ያህል ወታደር ግርማቸው አለበልና ከድር በድሩ የተባሉ እንደሚገኙባቸው የቆሰሉትም ወደ ህክምና እንደተወሰዱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።