Monday, August 17, 2015

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሙስሊም ፍትህ አፈላላጊዎች ላይ የገዥው መንግስት ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ተቃወሙ።



    እንደመረጃው ገለፃ በአዲስ አበባ ከተማ የገዥው መንግስት ተላላኪ የሆነው  ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሙስሊም ፍትህ አፈላላጊዎች ላይ የወሰደው የፍርድ ሂደት ፍትሃዊነት የጎደለውና ከዳኝነት ስነ-ምግባር ውጪ የሆነ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ ምሁራንና በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ ሰራተኞች በአፅንዖት እየተቃወሙት መሆናቸውን ታውቋል።
    ምሁራንና ሰራተኞች በዋናነት ትኩረት ካደረጉበትና ቅሬታ ካሰሙበት የሙስሊም ፍትህ አፈላላጊዎች ጉዳይ የተወሰነውን ለመግለፅ ያህል ተከሳሾች አሸባሪዎች አይደሉም የአሸባሪነትን መስፍርትም አያሟሉም መንግስት ዜጎችን አሸባሪ ለማለት ሊከተለው የሚገባው መለኪያ መኖር አለበት እንጂ እንደፈለገ በሚያሽከረክረው ፍርድ ቤቱ ንፁሃን ዜጎችን ማሰርና ማሰቃየት የለበትም በማለት መግለፃቸው ለማወቅ ተችሏል።