በመቐለ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው የህወሓት
ጉባኤ ለቡዙ አመታት በትግራይ ህዝብ ሲደርስ የነበረውን ችግሮች በማያዝ ያቀረቡት የአገር ሽማግሌ ወኪሎች እንደነበሩ የገለፀው መረጃው
በተለይም በመቐለ ከተማ በህጋዊ መንገድ የተሰጣቸውን መሬት አግባብነት በሌለው አስራር እየቀሙ በዲያስፖራ ስም መውሰድ ብዙ ህዝብ
ለችግር ተጋልጦ እንዳለ ክሱን ይዘው በመሄድ ባቀረቡበት ግዜ ይመለከታቸዋል የተባሉት አካላት “ ከዚህ ጉባኤ በኋላ እንፈታዋለን
“ በሚል የማስመሳያ ምላሽ እንደሰጧዋቸው ለማወቅ ተችሏል።
የህዝቡ ተወካይ የሆኑት የአገር ሽማግሌዎች ህዝቡ ከምርጫ በፊትና በኋላ
በመልካም አስተዳደር እጦት እየተሰቃየ ነው፤ ስራ አጥነት ከቀን ወደ ቀን ሲባባስ እንጂ ሲቀንስ አልታየም፤ የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች
በእኩልነት አይደለም ህዝቡን እያገለገሉት ያሉት፤ በአጠቃላይ የህዝቡ ምሬት ሰሚ ጀሮ አጥቶ እንዳለና ህዝቡም በመንግስት እምነት
አጥቶ እንዳለ በስብሰባው የህዝቡ ሃሳቦች ቀርበው እናየዋለን በሚል
አጥጋቢ የሆነ ምላሽ ሳይሰጣቸው እንዳለፈ ምንጮቻችን ጨምረው ገለፃል።