ባለፈው ግዜ በትግራይ ምእራባዊ ዞን አካባቢ የትጥቅ ትግል በሚያካሂደው
አርበኞች ግንቦት 7 ለተገደሉት የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ቤተሰቦች የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ ሑመራ ከተማ ለሚገኙ ባለሃብቶች
እያስገደዷቸው መሆናቸውንና በርካታ ገንዘብ ተዋጥቶ እየተሰበሰበ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ።
የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት በስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በወሰደው
የማጥቃት እርምጃ ከሞቱት ወታደሮች መካከል ኮለኔል ወልደሚካኤል የተባለ የሚገኝባቸው አዛዦች ለቤተሰቦቻቸው የሚሆን ገንዘብ የዞኑ
አስተዳዳሪዎች ከባለሃብቶች በግድ እየሰበሰቡ መሆናቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።