Wednesday, September 2, 2015

በአማራ ክልል በሰሜን ወሎና በጎጃም ተወላጆች መካከል በሁመራ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት 9 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።





በአማራ ክልል ሰሜን ወሎና በጎጃም ተወላጆች መካከል ስርዓቱ በፈጠረው ግጭት ምክንያት ነሃሴ 6/2007 ዓ/ም በሑመራ አካባቢ 9 ሰዎች መሞታቸውና በወል ያልታወቁ በርካታ ግለሰዎችም በከባድ መቁሰላቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ አስታውቋል።
    ሰብኣዊ ርህራሄ የሌላቸው የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች በግጭቱ ወቅት የቆሰሉት ሰዎች የጠላት ወገኖች ናቸው በማለት የሁመራ ከተማ አስተዳዳሪዎች በመፈረጃቸው በርካታ ቁስለኞች ለከፋ በሽታ መጋለጣቸውና ወደ ሩቅ አካባቢ ሄደው እንዲታከሙ መገደዳቸው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።