Sunday, September 20, 2015

በአፋር ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የወያኔ ኢ..ሀ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ስልጣንን መነሻ ያደረገ አለመስማማት በመካከላቸው መንገሱን ከስፍራው ምንጮቻችን ከላኩት መረጃለማወቅ ተችሏል።



በአፋር ክልል የሚገኙ የስሮኣቱ ባለስልጣናት ስልጣንን መነሻው ያደረገ ግጭት ፈጥረው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ቀደም ሲል ለ20 ዓመታት ያህል በስልጣን  የቆየው አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ በስርዓቱ ላይ እምነት የለህም በሚል ከስልጣኑ የተወገደ ሲሆን በምትኩ አቶ ጠሃ መሃመድ የተባለ ካድሬ በመቀመጡ አቶ እስማኤል ስላልተቀበለው አለመግባባቱ እንደተፈጠረ ሊታወቅ ተችሏል።
አቶ እስማኤል ባለፈው ዘመነ ስልጣኑ በህዝብ ላይ የደረሰው በድል ይፋ እንዳይወጣና ጥያቄ እንዳይጠይቀው ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ስልት መሆኑን አንዳንድ ታዛቢዎች ተናግረዋል።