Sunday, September 20, 2015

የጉጅሌው መሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለትምህርት ጥራት እንቅፋት መምህራን ናቸው ሲል ያቀረበው ሃሳብ በመምህራን ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱ ተነገረ።




በተለያዩ የስርዓቱ ሚዲያዎች በመቅረብ ለሃገራችን የትምህርት  ጥራት እንቅፋቶችና ተጠያቂዎች  መምህራን ናቸው ሲል የወያኔው መሪ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ያቀረበውን አጀንዳ መምህራኑ በበኩላቸው እንቅፋት እየሆነ ያለው ስርኣቱ ራሱ ነው እንጂ እንቅፋት እየሆነ ያለው ሲሉ ለአብነትም መምህራን ትምህርት አቁመው የፖለቲካ ስራ እንዲሰሩ የሚያስገድደው ኣንዱ ትልቁ ምክንያት ሲሆን በተለይ በትምህርት ድክመት ያለባቸውን ግለሰቦች ወደ ትምህርት ፅህፈት ቤት ማስገባት፥ ለመምህራን የሚከፈለው ደመወዝና አበል ዝቅተኛ መሆንና ከሃገሪቱ የኑሮ ሁኔታ ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ፥ ለመምህራን የመኖሪያ ቤት አለመሰጠቱ ለመማር ማስተማር ሂደቱ አጋዥ የሆኑ የሚያግዙ በቂ መጽሃፍት መገልገያወች አለመቅረባቸው  የሚሉትንና ሌሎችንም በመጥቀስ የመንግስት ድክመት መሆኑን በማስረገጥ ተናግረዋል።
ገዥው የወያነ ኢ.ህ.አ.ኢ.ዴ.ግ ስርዓት በትምህርት በኩል ያላቸው ዝንባሌ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ከሌሎች ሀገሮች ጋር ያለው ግንኙነት የሳከረ መሆኑን ሊታወቅ ተችሏል።