Sunday, September 20, 2015

የትህዴንን ድርጂት በሊቀ-መንበርነት ሲመራ የቆየው ሞላ አስገዶም መጭውን የድርጂቱ ድርጂታዊ ጉባኤ በመፍራት መክዳቱን የታዘቡ ታጋዮች የትግላችንን ውጤት ያፋጥነዋል ሲሉ 2008 አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በተከበረው በዓል ላይ በደስታ ገለፁ።



የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴንን ሲመራ የነበረው ሞላ አስገዶም በቅርቡ ሊካሄድ የተቃረበውን የድርጅቱን  ጉባኤ በመፍራት በተለያዩ ጊዜያት በወታደራዊ ስራዎች ላይ በፍርሃት በአንዳንድ የግል ጥቅም ፈላጊነትና በስልጣን ወዳድነቱ እንዲሁም በአመራርነት የብቃት ማነስ ሊገመገም እንደሚችል በመስጋቱ ምክንያት ራሱና ምንም የማያውቁ አባሎቹን ማጥቃት እናደርጋለን በሚል ስልጣኑን ተጠቅሞ በማደናገር ያደረገው እጂ ወደ ላይ እያለ መፈርጠጥ በርካታ የሰራዊቱ ታጋዮችን ያሳቀ ሲሆን ታጋዮቹ ለትግላችን የማንደራደርና የማንበረከክ የጽናት ተምሳሌዎች መሆናችንን በማወቁ እንኳን ፈረጠጠና ከጉባኤያችን ወጣልን “በጥባጭ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣ ነበር” ሲሉ መናገራቸውን   በየግንባሩ የሚገኙ ሪፖርተሮቻችን ገልፀዋል።
ሪፖርተሮቻችን አያይዘውም እንድገለፁት 2008 ዓ/ም አዲስ አመትን አስመልክቶ የአወት ንውፅዓትና የማዕበል የባህል ባንዶች በተለያዩ ግንባሮች ተዘዋውረው አዳዲስ የትግል ዜማዎችንና የተለያዩ ኮንሰርቶችን አቅርበዋል፣ የድርጂቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙበት ሲሆን                      የድርጂቱ ምክትል ሊቀመንበር ታጋይ መኮነን ተስፋይም ድርጂታዊ መግለጫ አሰምቷል።