Tuesday, December 1, 2015

በአማራ ክልል ምዕራብ እና ታች አርማጭሆ የሚገኙ ቤተ እስራኤላዉያን ነዋሪዎች የሆኑ ወገኖች ከፈደራል ፖሊስ ስለ በመጋጨታቸው የተነሳ የዜጎቻችን ሂወት ማለፉ ታዉቀዋል።



        በአማራ ክልል ታች አርማጭሆ ወረዳ በታጣቂዎች እና በፈደራል ፖሊስ እንዲሁም በቦታዉ በነበሩ ቤተ እስራኤላዉያን ከጥቅምት  28 2008ዓ.ም ጀምሮ ባጋጠመ ግጭት ከፈደራል ፖሊስ 10 ሲሞቱ ከሲቪሎች ደግሞ 20 ሰላማዊ ሰዎች ፈደራል ፖሊስ በተኮሱት ጥይት ሂይወታቸው ማለፉን ከቦታው ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
      መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው በወረዳዉ  ሰለማዊ ህዝብ እየጨፈጨፉ  የሚገኙ የፈደራል ፖሊስ አባላት የህዝባችን ተቃዉሞ ሊቆጣጠሩት  ባለመቻላቸው የተነሳ ሌላ ተጨማሪ ፍደራል ፖሊስ ከደባት እና እምባ ጊዮርጊስ ግጭቱ በተለኮሰበት አከባቢ እንደተላኩ ገልፀው እየፈፀሙት የነበሩት ወንጀል እንዳይታወቅ  በማለት ጋዜጠኛ ይሁን ሌላ ታዛቢ አካል ወደ ቦታው እንዳይሄድ እንደተከለከለ ህዝብ በበኩሉ መንግስት በታጣቂዎቹ አድርጎ እየጨፈጨፍን ነው በማለት በስርአቱ ያላቸው ጥላቻ በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታዉቀዋል።