Wednesday, December 16, 2015

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወተሃደሮች በሲቪል ሕብረተሰብ ላይ በሚፈፅሙት አጸያፊ ተግባሮች ምክንያት ህዝብ ከሚኖርበት ኣከባቢ ርቀው እንዲሰፍሩ ጥያቄ መቅረቡ ታወቀ።



    በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል በተለያዩ ኣከባቢዎች ሰፍረው የሚገኙ የገዥው የኢህአዴግ ስርአት ወተሃደሮች በሰነ ምግባር የታነፁ ባለ መሆናቸው በስቪል ህብረተሰብ ላይ በደል በማድረስ ላይ እንደሚገኙና ከዚህ በመነሳትም “እነዚህ ወተሃደሮች ሰላም ለማክበር የተሰለፉ ሳይሆኑ ለራሳቸው ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ግፈኞችና ሌቦች ሰለሆኑ ህዝብ ከሚኖርበት ኣከባቢ ርቀው እንዲሰፍሩ  በተደጋጋግሚ ኣቤቱታና ጥያቄ በማቅረብ ላይ መሆኑን ተገለፀ።
    ከዚህ በመነሳትም በውቅሮ ክልተ ኣውላእሎ ከተማ አከባቢ  ሰፍረው የነበሩ የ21 ክፍለ ጦር ወተሃደሮች ነዋሪው ህዝብ ሰለጠላቸው ከቦታው ለቀው በዴስአ በተባለው በረሃ እንዲሰፍሩ መደረጉ ታወቀ።