Saturday, January 16, 2016

በአዳማ ከተማ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ ተማሪዎች ምግብ አንበላም በማለት ኣድማ እንዳካሄዱ ታውቋል።



    ከስፍራው ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ በአዳማ በሚገኘው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  የሚማሩ ተማሪዎች  በኦሮምያ ክልል የሚካሄደው ህዝባዊ ተቋውሞ በመደግፍ  በገዥው የኢህአዴግ ስርአት ያላቸው ጥላቻ  በመቃወም፣ በዚህ ሳምንት የምግብ አድማ በማካሄዳቸው ምክንያት፣ የስርአቱ ባለስልጣኖች ደግሞ ያላስቡት የኣድማ አካሄዳቸው ያሰቀየራቸው በመሆኑ በላያቸው ምን አይነት እርምጃ እንደሚወስዱ  እንደጠፋቸው ለማወቅ ተቻለ።

 ተቃዋሚዎቹ አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርአት ሰለማዊ ወገኖቻችን በጥይት እየገደለ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ወገኖቻችን ደግሞ  አስሮ በማሰቃየት ስላለ፣ ይህ ህጋውነት የሌለው ተግባር እስካል ተቋረጠ ደረስ የምግብ አድማው እንደሚቀጥሉበት የተቋውሞው ተሳታፊዎች መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
   የዚህ አይነት የምግብ አድማ ተቃውሞ ወደ ሌሎች የሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች ተዳርሶ እንዲቀጥል ታላቅ ችሎታ እንዳለ መረጃው ጨምሮ ገልፀዋል።              

No comments:

Post a Comment