Monday, March 28, 2016

በኦሮምያ ክልል ነቀምት ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ባነሱት ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት ከ 100 በላይ አስተማሪዎች መታሰራቸው ከቦታው የደረሰን መረጃ አስታወቀ።



 በደረሰን መረጃ መሰረት በኦሮምያ ክልል ነቀምት ከተማ በመጋቢት 15 /2008 ዓ.ም ተማሪዎች ባነሳሱት የታቃዉሞ ሰልፍ ምክንያት ከ100 በላይ አስተማሪዎች መታሰራቸዉን ከገለፀ በኋላ፣ በተማሪዎቹ የተነሳ አንፃር ፀረ ህዝብ የኢህአዴግ ስርአት ያነጣጠረ ተቃዉሞ ካሰሙት ከነበሩ መፎክሮች፣ በከፍተኛ ባለስልጣናት በንፁሃን ዜጎቻችን በፀጥታ ሃይሎች እየወረደ ያለው በደሎች ይቁም የሚልና ሌላ ተመሳሳይ ድምፅ እያሰሙ እንደዋሉ ታዉቀዋል።
  በተማሪዎቹ በተነሳው ተቃዉሞ ተከትሎ ከፍተኛ አስተዳዳሪዎች እና የፅጥታ እካላት በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ከ100 በላይ አስተማሪዎች እናንተ ናቹ ለዚህ ተቃዉሞ እንዲነሳሳ ያደረጋቹሁት በሚል ምክንያት እንዳሰሩዋቸው መረጃው ጨምሮ እስረድተዋል።
 ከታሰሩት አስተማሪዎች መካከል ለመጥቀስ ያህል እመኑ የተባለ የባዮሎጂ አስተማሪ፣ አለማዮህ የተባለ የኬምስትሪ አስተማሪ፤ ኣጀጋ የፍዚክስ አስተማሪ፤ ለገሰ የተባለ አስተማሪና ሌሎች ባልዋሉበት ወንጀል መታሰራቸው ለማወቅ ተችለዋል።

No comments:

Post a Comment