Monday, March 7, 2016

በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች በብአዴን /ኢህአደግ አመራሮች በፈጠሩት የመልካም አሰተዳደር ችግር የተነሳ የካቲት 22/6/2008 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ ማደረጋቸው ተገለፀ።



በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የሚኖር ህዝብ በብአዴን /ኢህአደግ አመራሮች በፈጠሩት የመልካም አሰተዳደር ችግር የተነሳ፣ የካቲት 22/6/2008 ዓ/ም የ04፤ 03፤05 እና 01 ቀበሌ ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክር በመያዝ  ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ  ሲሆን፣ በሰልፉ ላይ ከያዝዋቸው መፈክሮቹ የተወሰኑትን ለመጥቀስ  ያህል፣ ፍትህ በገንዘብና በዘመድ ተቀይሯል፤ የአማራ ክልል ህዝብ መንግሰት የለውም፤ የአማራ ተወላጅ ከሌሎች  አጎራባች ክልል ህዝቦች ጋር እያጣላችሁ ነው የሚሉ መፈክሮች በመያዝ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳደረጉ ለማውቅ ተችሏል።
    ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የአማራ ህዝብ የኢህአዴግ ሰረአት ወደ ስልጣን  ከመጣ ጀምሮ ለ25 አመታት ያህል ምንም ለውጥ ሳያመጣ ችግሮቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እየሂዱ መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።


No comments:

Post a Comment