Monday, March 7, 2016

በምእራብ እዝ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ወታደሮች በተፈጠረው የህዝብ ተቃውሞ በመደገፍ አንታገልም ማለታቸው ተገለፀ።



የደረሰን መረጃ እንድሚያሰረዳው፣ በምእራብ እዝ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት የካቲት 18/6/2008 ዓ/ም  ከአምሳ አለቃ ማእረግ  በላይ በተደረገው ሰብሰባ በየሬጅመንቱ የሚገኙ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ  ወታደሮች፣  መንግሰት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን የመግደልና የእስራት  እርምጃ በመቃወም  አንታገልም አሰናብቱን በማለት አንድ አሰር አለቃ ከዲር የተባለ የባሌ ተውላጅ የሆነ ራእሱን በራሱ  ህይወቱን ያጠፈ ሲሆን፣ ሌሎች የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ወታደሮችን ሰብሰባው እንዳበቃ ከየሬጅመንታቸው በመውሰድ እስከ አሁን የት  እንዳሉ እንደማይታወቁ  ከሰፍራው የተላከልን መረጃ አመልክቷል።
   በእዙ የሚገኙ ወታደሮች  በአሁን ሰአት በከፈተኛ ሰብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኘ የገለፀው መረጃው፣ በመንግሰት እየተወሰደው ያለውን የመግደል እርምጃ ትክክል አደለም ብለው የተቃወሙ ወታደሮችን  እጃችሁ በህዝቡ አመፅ  አለበት በማለት ሂሰ አድርጉ እየተባሉ በግድ እየተገደዱ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ጨምሮ አሰረድቷል።






No comments:

Post a Comment