በመረጃው መሰረት የአድዋ ከተማ ነዋሪዎች ከሶስት አመት በፊት
ለመንገድ ማስፋፍያ በሚል ምክንያት ከማይ ዓሳ እስከ ዕዳጋ ዓርቢ የሚገኝ ቦታ ከ400 በላይ የመኖርያ ቤቶቻቸው ምንም ካሳ
ሳይሰጥ በመፍረሱና እስከ አሁን ድረስም ምንም አይነት ተለዋጭ መሬት
ባለመታደሉ እንዲሁም የገባበት ቃል መንግስቲ ባለመፈፀሙና የተባለው
ጎደናም ባለመሰራቱ ህዝብ ለአቧራና ለሌላ ተደራራቢ ችግር ተጋልጦ እንደሚገኘ ታውቀዋል።
መረጃው ጨምሮ በህዝቡ ላይ የወረደው ችግሩ ሊስተካከል ቀጣይ ለከተማው አስተዳዳሪዎች
አቤቱታ ቢያቀርብም እንኳ ተገቢ ምላሽና ፍትህ የሚሰጥ አካል በማጣቱ፣ የህዝቡ ምሬት
በከፋ መልኩ በመቀጠል ላይ መሆኑንና ህዝቡ አቤቱታ በሚያሰማበት
ግዜ የከተማው አስተዳዳሪዎችም በበኩላቸው ፅህፈት ቤታቸው በመዝጋትና በመደበቅ ላይ መሆናቸው፣ በተለይ ደግሞ ኪዳይ አፅብሃ የተባለ አስተዳዳሪ በሙስና ተዘፍቆ ሲያበቃ በፅህፈት
ቤቱ ስለማይገኝ ህዝብ የሚያስተናግደው አጥቶ ስራውን ትቶ በመንገላታት
ላይ እንደሚገኝ መረጃው አስረድተዋል።
No comments:
Post a Comment