Saturday, March 12, 2016

በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ የአማራና የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ዜጎች በኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸው ታወቀ።



    የደረሰን መረጃ እንደገለፀው፣ በኢህአዴግ  ሰረአት ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ምክንያት  የተነሳ፣ በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ ዞን የሚገኙ የአማራ ተወላጅ የሆኑት አቶ ደምሰው አሰፋና ጌታቸው አሰፋ የተባሉ ወንድሟሟቿች የተገደሉ ሲሆን። ከትግራይ ተወላጅ ደግሞ መብራቶም  ማዓሾ የተባለ ግለሰው በጩቤ ሰውነቱን በመተልተል ህይወቱን ያሳለፉት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አሰረድቷል።
   የገዢው የኢህአዴግ አገዛዝ መጥፎ አሰራር ምክንያት  የተነሳ የአንዱ ክልል ብሔር ወደ ሌላው ክልል  ተንቀሳቅሶ  እየሰሩ ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦች ንብረታቸውን በማቃጠልና በመንጠቅ በአሰቃቂ የአገዳደል ሁኔታ ህይወታቸውን ያለፈ  መሆኑን ምንጮቻችን ከሰፈራው የላኩልን የመረጃ ገለፀ።

No comments:

Post a Comment