ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው ።በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ
ወረዳ የሚገኙ የኦሆዴድ አመራሮች ህዝቡ በሚያደርገው አመፅ እጃቸው አለበት የተባሉት ባለሰልጣኖች የካቲት 23/6/2008 ዓ/ም አቶ አለሙ ደጉማ የወረዳ ዋና አሰተዳደር የነበረው
አቶ መልኪ ቶሎሳ የ02 ቀበሌ ሊቀመንበር የሆነው አቶ አስቻለው ግድሳ የኦሆዴድ የድርጅት አባል የነበሩትን ሰዎች ያለ በቂ ምክንያት ለሊት ከመኖሪያ ቤታችው በመወሰድና እስከ አሁንም
ድረስ የት እንዳሉ እንድማይታውቁና ቤተሰቦቻቸው በተደጋጋሚ ሰለ ሁኔታው
ለሚመለከተው የመንግስት አካል አቤቱታ ቢያቀርቡም መልሰ የሚሰጣቸው
አካል እንዳላገኙ የደረሰን መረጃ ገልፀዋል።
ገዢው የኢህአዴግ ሰርአት በኦሮሚያ ክልል እየተቀጣጠለ ያለው የህዝብ ተቃውሞ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት በኦሆዴድ ድርጅት አመራሮችና አባሎች ላይ ከሃላፊነት የማውረድና የማሰር እርምጃ
እየወሰደ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment