ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት፣ በትግራይ
ክልል ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ የፍትህ አካላት ሰልጣናቸውን ተጠቅመው በህዝብ ላይ በተለያዩ መልኩ የሚገለፅ ሙስና እያካሂዱ እንዳሉ
በነዋሪው ህዝብ የተከሰሱ በርከት ያሉ ሆነው፣ እንዲሁም የተወሰኑትን ለመጥቀሰ ያህል የምስራቅ ዞን የፅፈት ቤት ሃላፊ የነበረው አቶ ሰለሞን የሚባል እንደሆነና ቀደም ሲል ከስልጣኑ እንደታገደ
የሚታውቅ ሆኖ፣ በአሁን ውቅት ደግሞ በእዚሁ ፅፈት ቤት ምክትል የነበረው
አቶ ገብረ ሰላሴ የሚባል የተባረረ እንደሆነ ታውቋል።
እንዲሁም የእዚህ ዞን የፀጥታ አሰተዳደር ሃላፊ የነበረው ከሰልጣኑ ታግዶ
እንዳለ ከገለፀ በኃላ፣ ከሃላፊነቱ የታገደበት ምክንያት ደግሞ ሙስና
ሆኖ፣ በፈፀመው ከሃላፊነት ውጪ በመጠቀም የተነሳ በህዝቡ ክስ ቀርቦበት
በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ለማውቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment