Friday, March 25, 2016

በምእራብ ዞን የሚገኙ አመራሮች በፈፀሙት የሙስና አሰራር የተነሳ ህዝብ እየተቃወመ ከስልጣናቸው እያስወገዳቸው መሆኑ ተገለፀ።



 በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ እንደሚገልፀው፣ በትግራይ ክልል በምእራብ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ በህወሃት /ኢህአዴግ ገዢው ሰርአት የሾማቸው አመራሮች  በሙስና አሰራር ህዝብን ሲያሰቃዩ የቆዩ ሃላፍነት የማይሰማቸው አስተዳዳሪዎች     በአሁን ወቅት በዚህ ዞን የሚገኙ ህዝቦች ባካሄዱት  ሰፊ ተቃውሞ ከስልጣናቸው ይነሱ የሚል ባቀረበው ጥያቂ መሰረት ከስልጣናቸው መባረራቸው ተገለፀ።
  የደረሰን መረጃ ጨምሮ እንደሚያሰረዳው፣ ሰልጣናቸውን ተጠቅመው የግል ጥቅማቸውን በማሰቀደም ህዝብን ሲበድሉ ከቆዩት የተወሰኑትን ለመጥቀስ፣  የወረዳ ዋና አሰተዳዳሪ  የነበረው ዮውሃንስ 150 ሔክታር መሬት ሰልጣኑን ተጠቅሞ የግል ጥቅሙን ሲያውል እንድቆየ በህዝብ እንደተረጋገጠ እና እንደተባረረ እንድሁም ሰሰን ካሕሳይ የገጠር መሬት ሃላፊ ሆኖ ሲሰራ በቆየበት ጊዜ ከግል ሃብታሞች ጋር በመሰማማት የማይገባውን ጥቅማጥቅም ለግሉ ሲያውል እንደቆየ ከቦታው የደረሰን መረጃ መሰረት ለማውቅ ተችለዋል።



No comments:

Post a Comment