Monday, March 21, 2016

በምስራቃዊ ዞን የሚኖር ህብረተሰብ በተፈጠረው የመልካም አስተዳደር እጦትና ብልሹ አሰራር ምክንያት፣ የመሰረተ-ልማት ፍትሃዊ አሰራር በማጣቱ ህዝቡ በማማረር ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገለፁ።



        በትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ የሚኖር ህዝብ የሚጠጣ ጥራቱን የጠበቀ ውሃ ካጣ ብዙ አመታት እንዳስቆጠረ ከገለፀ በኃላ፣ ይሁን እንጂ በዞኑና ወረዳው የሚገኙ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የህዝቡ ጥያቄ ሊመልሱ ባለመቻላቸው የተነሳ፣ በአሁኑ ጊዜ ነዋሪው ህዝብ በውሃ እጦት ምክንያት እጅግ ተቸግሮ  ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ በመጠቀም ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች እየተጋለጠ እንዳለ ተገለፀ።
  በተጨማሪም በወረዳው አጋጥሞ ያለውን ለድርቅ የተጠቁ ወገኖች እንዲውል ተብሎ በለጋሽ ድርጅቶች የመጣውን እህል በአስተዳደሮችሁ ለተጎጂው ህዝብ ከማከፋፈል ይልቅ ከግብረ አበሮቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን፣ ተካፍለው እየበሉት ስለሚገኙ በድርቅ የተጎዳውን ህዝብ በርሃብ በመሰቃየት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
      እንዲሁም በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ የሚገኙ አስተዳደሮች በወረዳው ለሚገኙ በድርቅ የጠቃቸው ሰዎች እንዲውል ተብሎ ከለጋሽ አገሮች የተገኘ እርዳታ ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት የታዘበው ነዋሪ ህዝብ፣ መንግስት መልካም አስተዳደር አነግሳለሁ እያለ መዶስኮር እንጂ በተግባር የሚሸረፍ ፍትሃዊነት ያለው አሰራር አልሰራም፣ ችግሩን በከፋ መልኩ  እየተባባሰ እንደሚገኝና የኦሮሞ ህዝብ እያካሄደው እንዳለው ተቃውሞ እናካሂዳለን በማለት የስርአቱን የተዛባ አሰራር እየተቃወመው መሆኑን መረጃው አክሎ ጠቅሰዋል።

No comments:

Post a Comment