በክልል ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ስብሰባ የካቲት 26 2008 ዓ/ም የጀመረ
ሲሆን፣ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ አመራሮችና ካድሬዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ የስብሰባው አጀንዳም ባለፉት ሳምንቶች መልካም አስተዳደር
አስመልክቶ በተካሄደ ህዝባዊ ግምገማ በህዝቡ ዘንድ ተነስተው የነበሩት ሃሳቦች በመተግበር ላይ ስላልሆኑ፣ ህዝቡ ደግሞ የህወሓት/ኢህአዴግ
መሪዎች በአፋችሁ እንጂ በተግባር ላይ የለም በሚል በድጋሜ አቤቱታቸውን በማሰማት ላይ ስላለ ምን ሁነን ነው ቃል የገባነለት የማንተገብረው
የሚል ስብሰባ እንካ ቢሆንም፣ በሚያካሂዱት ያለውን ግምገማ ላይ መረዳዳት ስለሌላቸው ኣያንዳንዱ አርእስት ያለምንም መቛጫ እያለፉት
ኣንደሚገኙ ታወቀ።
ኣያካሄዱት ባለው ስብሰባ ላይ ኣያተነሱት ካሉ ነጥቦች፣ በተካሄደው ህዝባዊ
ኮንፈረንሶች ለእርዳታ የመጣ ስንዴ አስተዳደሮች ራሳችሁ ናችሁ የበላችሁት፤ ማዳበሪያ በአስገዳጅ ውሰዱ እያላችሁ ህዝቡን አከሰራችሁት፤
መልካም አስተዳደር በአስተዳደሮች አጥተናል፤ ወዘተ በማለት የገመገሙት ሰዎች የኣስራትና የማስፈራራት እርምጃ በአስተዳደሮች ተጀምሮ
ያለውን ለስርአታችን ወደ ባሰ አደጋ እያመራው ነው በሚል ተነስቶ ወደ ግለሰዎች ሊጠጋ ሲጀምር፣ በአመራሩ ውስጥ ከፍተኛ መሳሳብ
ተፈጥሮ እንደቀጠለ ከመረጃው ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው በመጨረሻ፣ በአክሱም ከተማ እያተካሄደ ባለው ስብሰባ የምስራቃዊ
ዞን የፍትህ ሃላፊ አቶ ሰለሞን የተባለው ከስራው ታግዶ እንዳለ፣ ኣንዲሁም ከአድዋ ከተማ ስሟቸው ለጊዜው ያልተጠቀሱ አስተዳደሮች
ከስራቸው የታገዱ እንዳሏቸው በአስተዳደሮች የስልጣን መዋቅር የፈጠረው ውጥረትና ያለመስማማት ተፈጥሮ እንዳለም አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment