Wednesday, March 16, 2016

በትግራይ ምእራባዊ ዞን ሁመራ ከተማ የሚኖሩ ሰዎች የአኢህ አዴግ ካድሬዎች በወልቃይት ጸገዴ እየተካሄደ ባለው ተቃውሞ አነሳስታቸዋል፤ የገንዘብ እገዛ አድርጋችዋል እየተባሉ የማስፈራራት ዛቻ ሲደርስባቸው ከቆየ በኃላ፣ በመርዝ እየተመረዙ በመገደል ላይ እንዳሉ ታወቀ።



በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ኣንደገለፁት፣ በሁመራ ከተማ የሚኖሩ ከገዢው የኢህአዴግ ስርአት ጋር ትስስር የለላቸው ባለሃብቶች፣ በወልቃይት ፀገዴ እየተነሳ ያለው አስተዳደር መሰረት ያደረገ ተቃውሞ በገንዘብ በማገዝና መማነሳሳት ተሳትፋችዋል ኣየተባሉ በአስተዳደሮች ከተመዘገቡ ከቡዞዎችሁ ውስጥ፣ ሽሙየ ገብሩ ለተባለው ሰው ተቃውሞውን ለመደገፍ 3ሺ ብር አዋጥተሃል በሚል የኣስፈራራት ዛቻ ሲደርስበት ከቆየ በኃላ። የካቲት 25 ቀን 2008ዓ/ም በሚተጥበት ሃይላድ ውሃ መርዝ በማድረግ ኣንደገደሉት ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩልም፣ በሁመራ ከተማ በወልቃይት ፀገዴ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ትክክል አይደለም በሚል በገዚው ስርአት ካድሬዎች የተቀነባበረ ሴራ ባለፈው ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን፣ በሰልፉ ላይ ከሌላ አካባቢዎች የመጡ መጤ ሰዎች የተሳተፉበት እንጂ የአካባቢው ተወላጆች በሰልፉ ላይ እንዳልነበሩ መረጃው አክሎ ያስረዳል።

No comments:

Post a Comment