Wednesday, March 16, 2016

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች በኢህአዴግ አንመራም በሚል የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ እንዳሉ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት፣ በአኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ፤ አምቦ፤ አርጆ፤ አርሲና አካባቢዋ የሚገኘው መላው ህብረተሰብ፣ ከያካቲት 24 ቀን 2008ዓ/ም ጀምሮ በየቀኑ በሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው የኦሆዴድ/ኢህአዴግ ስርአት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰው ያለ በደሎች ማስቆም አለበት፤ በአኦሆዴድ/አኢህ አዴግ አንመራም፤ የገዢው ስርአት ባለስልጣናት ከስልጣናችሁ ውረዱና ህዝባዊ መንግስት የመስረት የሚሉ መፎክሮች በመያዝ ሰልፍ እያካሄዱ መሆናቸው ተገለፀ።
መረጃው አክሎ፣ የአኦሮሞ ህዝብ ከአዲስ አበባ ማስተር ጋር በተያያዘ የጀመረውን ተቃውሞ ከሰዎስት ወር በላይ ያስቆጠረ ሲሆን፣ አሁንም በይበልጥ ሁኔታውን ተባብሶ ከጫፍ እስከ ጫፍ የክልሉ አካባቢዎች ተሳስሮ እንደሚገኝና በዚህ ተቃውሞ የተነሳም ለገዢው የአኢህ አዴግ ስር አት ስጋት ፈጥሮለት እንዳለና፣ በአንድ አንድ የክልሉና  የኦሆዴድ ባለስልጣናት ተቃውሞውን ለመግታት የበኩላችሁ ስራ አልሰራችሁም የተባሉት ከሃላፊነት ደረጃቸው የወረዱ እንደሚገኙ መረጃው በማከል አስገንዝቧል።

No comments:

Post a Comment