ምንጮቻችን ከቦታው የተላከልን መረጃ እንዳመለከተው፣ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቦረና
ወረዳ በሚደረግ ከፍተኛ እርዳታ የምልመላ አድሎነት የተነሳ የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ሓሰን
ሙህዲን የተባለው ግለሰው በተደጋጋሚ በህዝብ ላይ በሚፈፀመው በዝምድና እና በሙሰና አሰራሩ ምክንያት፣
የካቲት 7/6/2008 ዓ/ም ከሌሊቱ 4፣00 ሰአት አካባቢ ያሲን ተሰማ የተባለው ግለሰው በመኖሪያ ቤቱ በመሄድ ምንም
የሚበላ የሚቀመስ ሳይኖረኝ ከእኔ የተሻለ ሰው መዝግበዋል በማለት በጥይት ተኩሶ የገደለው መሆኑን ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ ለማውቅ ተችሏል።
በአገሪቱ ተፈጥሮ ባለው ድርቅ ምክንያት በሚደረገው የእርዳታ ምልመላ አድሎነት፣
በአማራ ክልል ብቻ የተከሰተ ሳይሆን በመላ አገሪቱ የሚታይ ኢ-ፍትሃዊነት አሰራር መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ምንጮቻችን
ጨምርው ገለፀዋል።
No comments:
Post a Comment