ምንጮቻችን እንደገለፁት፣ የሃረር ከተማ ነዋሪ ህዝብ ቀደም ሲል በውሃ
እጥረት ምክንያት እየተሰቃየ የነበረ ሲሆን፣ በተለይ ደግሞ ከህዳር 27 2008ዓ/ም ጀምሮ ኣስከ አሁን ድረስ በከተማዋ የሚኖር
ህዝብ ከተለመደው በከፋ መልኩ የምጠጥ ውሃ እጠረት አጋጥሞት እንደሚገኝና፣ ለዚህ ችግር ደግሞ መፍትሄ ለማደረግ መንግስት ኣንደተለመደው
የፕሮፖጋንዳ ስራው መስራት ያለፈ ለከተማው ነዋሪ ህዝብ የሚጠቅም ስራ እየሰራ እንደማይገኝ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ።- የከተማው ህዝብ ለእለታዊ ክንውኑና ለቁርስና ለምግብ
ቤቶች ማሳለጫ የሚሆን ውሃ ከተለያዩ ሃብታሞች በውድ ዋጋ ጥራቱን ያልጠበቀ በመግዛት ላይ ኣንዳለና፣ ለዚህ ደግሞ መንግስት እያየና
እየሰማ መፍትሄ ሳያደርግለት ሲቀር የድርጅቶች ባለቤት ያነሳሱትን ሰላማዊ ሰልፍ በከተማዋ ለማድረግ ፊርማ እያሰባሰቡ እንደሚገኙና
ነዋሪ ህዝብም ከጎናቸው በመሆን አዛችሁ በማለት ላይ እንደሚገኝ ታወቀ።
No comments:
Post a Comment