Saturday, March 19, 2016

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ራያ አላማጣ ወረዳ የሚገኙ ታጣቂ ምልሻዎች በህዝብ ላይ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው በላኩልን መረጃ ታውቀ።



  ምንጮቻችን እንደገለፁት፣ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ራያ አላማጣ ወረዳ ሸኮማጆ ቀበሌ የሚገኙ የገዢው የኢህአዴግ ታጣቂ ምልሻዎች በህዝብ ተቀባይነት ሰለሌላቸው የካቲት 21/2008 ዓ/ም ሊነጋጋ ሲል  በአካባቢው ህዝብ ላይ በደል ሲያደርስ የቆየ ታጣቂ ምልሻ   ሃለቃ ብስራት ዳኛው የተባለ ሰው በጩቤ በከባድ ተውግቶ እንደተገኘ ከቦታው ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ገለፀ።
   መረጃው ጨምሮ እንደገለፀ፣ በዚህ ሸኮማጆ ቀበሌ በተደጋጋሚ በእነዚህ ታጣቂ በምልሻ ሲደርስ የቆየው ከባድ በደልና ማሰፈራራት  ለወረዳ ፅፈት ቤት ማመልከቻ ቢያቀርብም እንኳ፣ የሚሰማ የመንግስት አካል በማጣጣታችው የተነሳ እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደደ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።

No comments:

Post a Comment