በትግራይ ክልል በምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በቂ የሆነ ጥራት ያለው ምግብናና ንፁህ ውሃ ባለማገኘታቸው ምክንያት በርከት
ያሉ ተማሪዎች ለተለያዩ በሺታዎች እየተጋለጡ በመሆናቸውና ደረጃው የጠበቀ የህክምና አገልግሎት በውቅቱ ሰለማያገኙ ለረዥም ጊዜ በበሺታው ተኝተው እየተሰቃዩና ከትምህርታቸው በማቑረጣቸው ተከትሎ ለተለያየ የአካል ጉዳትና
የሞራል ውድቀት የደረሰባቸው ተማሪዎች በተደራጀ መልኩ ጥያቂያቸውን ቢያቀርቡም፣ ተገቢ መልስ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ለማውቅ ተችሏል።
የደረሰን መረጃ እንዲሚያሰረዳው፣ እነዚህ ተማሪዎች በምግብና በንፁህ ውሃ ችግር በጠቅላላው በማህበራዊ አገልግሎት በዩኒቨርስቲ
እንድፈታ በተደጋጋሚ እያቀረቡ ጥያቄያችን ለምንድን ነው የማይፈታው? በዚህ ዩኒቭርቲ ለመማር ነው እንጂ በበሺታ ለመሰቃየት አልመጣንም፣ ትምህርት
እንዳንማር በአሰተዳዳሪዎች ችግር እየተናነቅን ነው የሚልና ሌሎችም
ጥያቂዎች ቢያቀረቡም የዩኒቭርስቲው የበላይ አመራሮች እንዲፈታ ከማደርግ ይልቅ አርፋችሁ ተማሩ ከዚህ ያለፈ ተማሪ የሚያነሳሳ ከሆነ
ግን እናባርራለን የሚል መልስ የሰጧቸው መሆኑን ለማውቅ ተችሏል፣
No comments:
Post a Comment