የደረሰን መረጃ እንደሚገልፀው፣ የደቡብ ክልል ህዝቦች ከምባታ ዞን ሸሽቾ
ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በመዳሃኒት እጥረት ለተለያዩ አደጋዎች የሚጋለጡ
ሆነው፣ በተለይ በዚህ ወረዳ ያለ መለስተኛ የሆነ ሆሲፒታል ንፅህናቸው ያልጠበቁ የህክምናን መሳሪያዎች ስለሚጠቀሙ፣ እናቶቻችን በወልድ ጊዜ ወደ ህክምና በሚሄዱበት
ንፅህና ያለው የህክምና መሳሪያ የሚገለገሉበት ባለመኖሩ፣ እነዚህ እናቶችና ህፅናት በርከት ላሉ ችግሮች እየተጋለጡ እንዳሉ አንድ ሰሙን ለመጥቀስ ያልፈለገ የአካባቢው ነዋሪ የሆነው ግለሰብ በምሬት
ገለፁ።
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው፣ በተለይ ችግሩ ከጥቅምት ወር 2008 ዓ/ም ጀምሮ
እስከ አሁን ደረስ እየታየ ቢሆንም የጤና ደርጅት መጥፎ አስራር እየተበላሸ
እየሂደ እንዳለና የመዳሃኒት በመጥፋቱ ወደ ከፍተኛ ሆሲፒታል ለመሄድ ገንዘብና ጉልበት እናጠፋለን ሲሉ የአካባቢው ነዋሪ ምሬታቸውን በመገለፅ ላይ ይገኛሉ።
No comments:
Post a Comment