Monday, March 21, 2016

የኢትዮጵያ ህዝብ እያካሄደው ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ የተወሰደው እርምጃ የመከላከያ ሰራዊቱን ስሜት ለማወቅ በተደረገው ሰፊ የምክክር መደረክ፣ ሁሉም የሰራዊቱ አባላት ሃሳቡን እንደተቃወሙት ተገለፀ።



     የአዲስ አበባን ማሰተር ፕላን ተከትሎ በመላው የኦሮሚያ ከተሞችና ገጠሮች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት የስልጣኑን ህልውና ለማረጋገጥ ሲል  መሳሪያ ካልያዘው ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርግ ህዝብ ላይ ለመበተን እያካሄደው ያለውን ጭፍጨፋ በርከት ያለው የሰው ህይወት በጥይት የረገፈ ሲሆን፣ ለዚህ ኢ-ፍትሃዊ ያሆነውን እርምጃ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚገኙት ድርጅቶችና ሙሁራን በጥብቅ በመኮነን የተነሳ፣ በከባድ ጭንቀትና ስጋት የወደቁ የስርአቱ መሪዎች፣ በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው ስሜት ለማወቅ የካቲት 23 /2008 ዓ/ም ሰፊ ምክክር ለማካሄድ በተደረገው ስብሰባ  የተወሰደውን እርምጃ በሰራዊቱ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል።
       በሁሉም የገዢው የኢህአዴግ መከላከያ ሰራዊት የተካሄደው ምክክር፣ ሰራዊቱ በሰላማዊ ሰልፍ በወጣው የኦሮሞ ህዝብ ላይ የተወሰደው ኣርምጃ በመኮነን፣ እንዲህ ያለ ግፍ በመንግስት ትእዛዝ በህዝባችን ላይ እየተወሰደ እኛ ለማን ነው የምንጠብቀው እየተንከራተትን ያለን በማለት በአንድ ድምፅ ሃሳቡን እንደተቃወሙት መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።



No comments:

Post a Comment