የደረሰን መረጃ እንዳስረዳው፣ የኢህአዴግ መከላክያ
ሰራዊት ከዉትድርናው እየሸሹ በየግዘው ባለማቋረጥ እየጠፉ መቖየታቸው የሚታወቅ ሆኖ፣ በተለይ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በመላው የአገራችን
አከባቢዎች አጋጥሞ የሚገኘው መፍትሔ ያጣ ግርግርና ግጭት ተፍጥሮ ባለበት ግዜ በተጨማሪም መከላክያ ሰራዊቱ ከዉትድርናው እየሸሸ
በመረጠው መንገድ እየሄደ በመገኘቱ የሰራዊቱ የሰው አቅም ተመናምኖ እንደሚገኝ ታዉቀዋል።
ከፍተኛ የመከላክያ ሰራዊቱ አዛዦች ለተመናመነው የሰው አቅም ለመተካት በሚል
ምክንያት፣ ባለፉት አመታት በመባረርና በመሰናበት ከዉትድርናው የወጡትን ሰዎች፣ አዲስ ለቤት መስርያ የሚሆን ቤት ይሰጣቹሃል፤ ወደ
ሰላም አስከባሪ ሃይል ትላካላቹ የሚሉ የተለመደ የመደናገርያ መላ በመጥቀም፣ ወደ ሰራዊት እንዲመለሱ በጠየቁበት ጊዜ የሚቀበላቸው
ሰው በማጣታቸው፣ በመስፈራራትና በግዴታ እንዲገቡ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment