Monday, March 7, 2016

የሴቶች መብት በህወሓት ኢህአዴግ አይረጋገጥም



  ሴቶች የህብረተሰቡ ግማሽ ኣካል መሆናቸውን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ቢሆንም በነበሩት የስርአቱ አምባገነን መሪዎች ግን ሴቶች በፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊና ማሕበራዊ  ህይወት ውስጥ  በህብረተሰቡ በእኩል ዕድላቸው እንዳይጠቀሙና በአደባባይ ወጥተው ድምፃቸው እንዳያሰሙ  መብታቸው  ታፍኖዋል።
     በመሆኑም  በላያችው ላይ  ተጭኖ ያለው መከራና ስቃይ ለማስወገድ ልክ እንደ ሌሎች ጭቁን ዜጎች  ለዴሞክራሲያዊ መብታቸው፤ ለማህበራዊ ፍትህ፤  ለእኩልነት፤ ለስላም  በኢኮኖሚው  እድገት  ለማረጋገጥ  ብለው  ባካሄዱት የ17 አመት  የትጥቅ ትግል፣  የሃገራችን ሴቶች በተለይ ደግሞ የትግራይ ሴቶች ጀግንነት  የተሞላበት ትግል በማካሄድ  ድሉን ለማምጣት ሲሉ መሰዋእት ከፍለው ኣካለ ሰንኩል  ሆነዋል።
      በዚህ መሰረት የሃገራችን ሴቶች ለመብታቸውና ለጭቁን ህዝብ ብለው ተፈጥራዊ ተፅእኖ ሳይበግራቸው፣ በሁሉም አከባቢዎች  በመሰማራት  ትግል የሚጠይቀው ግዳጅ  በመፈፀም   ከወንዶች ጓዶቻቸው ጋር በመሆን  ታጥቀው  ፊት በመምራት፣  የትግል ጀግኖች ተብለው ተሰይመዋል።

    የሀገራችን ሴቶች በተለይ ደግሞ የትግራይ ሴቶች ይህ ሁሉ ከባድ መስዋእት ከፍለውና አካለ ጎደሎ  በመሆን ጀግንነት ፈፅመው  ለድል ሲበቁ፣ የትግላቸው ፍሬና የመስዋእነታቸው ዋጋ  በፀረ ህዝብ  የህወሕት ኢህአዴግ ስርአት  የተገኘው ድልም ውጤት ኣልባ ሆኖ በመቅረቱ፣ በዚህ ሳብያም  አሁን እነዚህ ታጋዮች ለተደራራቢ ችግር ተጋልጠው መከራ የተሞላበት  ህይወት በመምራት ላይ ይገኛሉ።
  በእርግጥ ሁሉም ጭቁን ህዝብ ባካሄደው ከባድ ጥረት  የ17 አመት ትግል ፍሬ ሊያገኝ ያልቻለ የህብረተሰቡ ግማሽ አካል የሆኑት ጭቁን ሴቶችም ቢሆኑም  ለብቻቸው እርባና ሊያገኙ አይታሰብም።

   ይህ ሁሉ ለሴቶችና ለመላው የሃገራችን ህዝብ  የወረደው ግፍ ኣስቃቂ በመሆኑ ሴቶችም ልክ እንደሌላው የህብረተሰቡ ክፍል  መብት አልባ ሆነው በህወሓት  ኢህአዴግ ስረአት  ድርብርብ ጭቆና ተጭኖዋቸው ለከፋ ኑሮ፤ ሰደት፤ ረሃብ፤ ህመም፤ እስር ቤትና  ሞት ተጋልጠዋል። ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ በሀገራችን ያለው ስርአት  በሚፈፅማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ስራ አጥነት የወለደው የማሕበራዊ ኑሮ  ችግርና ሌላ ጉዳትን  ተጨምሮ ሴቶች  ይህን ለመቋቋም ባለመቻላቸውና ከዚህ የከፋ  የፈለገው ችግር ይምጣ በማለት፣ በረሀና ባህር  ኣቋርጠው ወደ ስደት በሚጓዙበት ግዜ የሚያሰቅቅ አመፅና ወርደት እየደረስባቸው  ይገኛል።  
      ለመጭው እድላቸው ቢሆንም በነፃነት ለመብታቸው እንዳይከራከሩና እንዳይደራጁ  እንዳይፅፉ  በስመ  ማህበር፤ ሊግ፤ የሴትች  ፈደርሽን፤ የመለስ ማሰልጠኛ ኣካዳሚ ወዘተ በሚሉ የማታላያ ስልታዊ ስሞችን  በመጠቀምና በመቀሰቅስ  በአረመኔው  ስርአት ስር ወድቀው ሳይወዱ በግድ እንዲሄድ በማስገደድ  ጭቆናቸው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
   በመሆኑም  ደግሞ  ለፍትህ፤  ለሰላም ለዲሞክራሲያዊ መብት፤  ለእኩልነት፤ መቻቻል እንዲሰፍን የተካሄደው  የትጥቅ ትግል ተክዶ    ለጥቂቶች የግል ጥቅም በመዋሉ፣  በዚህ ሳብያም ኣፈናና የተበላሸ አስተዳደር ተስፋፍቶ  ሃገርና ህዝብን  ወደ ውድቀት፤  ግርግር፤   መከፋፈል፤ እንደዚሁም ንፁሃን ዜጎች  በየቀኑ  በየጎደናው ህይወታቸው እያጡና  ኣብዛኞቹ  ደግሞ ባልዋሉበት በወንጀል  ክስ ስለሚቀርብላቸው፣  በፅጥታ ሃይሎች እየተደበደቡ ወደ  እስር ቤቶች ሲገቡ  የሴቶች የስቃይ ኑሮ   የከፋ  ሆነዋል።
  ምክንያቱም ሴቶች ሲባሉ የህብረተስቡ ሁለተናዊ ማህበራዊ ህይወት  በመሆናቸው፣ ለ25 አመታት ያህል በሁሉም ዜጋ  በተለይ ደግሞ በሴቶች ሲፈፀም የቆየውና  ያለው ግፍና የሰብአዊ መብት ጥሰት  ዛሬም ደርሶ የሚፈጠረ ለውጥ ሰለሌለ፣ አሁንም ዴሞክራሲያዊ ለውጥ  ለማምጣት ለሆዳቸው ብቻ የቆመው የህወሓት ኢህአዴግ ስርአት ለማሰወግድ  በሚካሄደው  ብረታዊ ትግል ፆታ ሳንለያይ ተሰልፈን ግዴታችንን በመፈፀም  ከጭቆና ልንላቀቅ ይገባናል።



No comments:

Post a Comment