Wednesday, March 16, 2016

በደቡብ ህዝቦች ክልል ከምባታ ዞን የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያለ ህጋዊ መንገድ በስርአቱ ካድሬዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አሳወቁ።



ምንጮቻችን እንደገለፁት፣ በደቡብ ህዝቦች ክልል ከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኙ የአንድነት ተቃዋሚ ድርጅት አባላት የሆኑት ሰዎች፣ የፈጸሙት ወንጀል ሳይኖራቸው ያለ ህጋዊ መንገድ ከየ ቤታቸው በማደን በፖሊስ አስገዳጅነት ወደ ከተማዋ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰዱ በመታሰር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በዚህ መሰረት ደግሞ፣ አቶ ደበበ እሸቱ፤ አቶ ፋሲል ኩራባቸውና አቶ ሲራክ ካሳ የተባሉት ወገኖች የካቲት 22 2008ዓ/ም ከየቤታቸው በፖሊስ ታድነው ወደ ከተማዋ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን፣ ይሁን እንጂ የካቲት 23 ቀን 2008ዓ/ም ቤተሰቦቻቸው ተሰባስበው ወደ ፖሊስ ታቢያው ፅህፈት ቤት በመሄድ ሁኔታውን ለመጠየቅ በሄዱበት ጊዜ፣ ችግር የለም የጉንቦት 7 አብላት ሆነው ስለተገኙ ወደ ዞኑ ፅህፈት ቤት ልከናቸዋል ቤታችሁ ተመለሱ እንደተባሉ እስከ አሁን ደረስ ደግሞ ታስረው የተወሰዱት ወገኖች አድራሻቸው እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።


No comments:

Post a Comment