Saturday, March 12, 2016

የህዝቦች ጥያቄ በብረት ሃይል አይታገድም!!



በአንድ አገር ዉስጥ የሚገኝ ገዢው ኢህአዴግ ስርአት እያስተዳደርኩት ነኝ ከሚለው ህዝብ ጋር  የሚኖረው ቀጥታዊ  ስምምነትና  ፖለቲካዊ  ውህደት  የሚስማማ ከሆነ፣  የህዝብን      ጥቅምና  ፍላጎት በማረጋገጥ  ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ የሚያጠያይቅ አይደለም፣ ምክንያቱም በህዝብ ላይ  ፖለቲካዊ መረዳዳት  ካለ  ገዥው ስርአት ከህዝቡጋር ያለው ግንኙነት፤ ፖለቲካዊ መረዳዳትና፤ መረጋጋት  ሊያሰፍን ሰለሚችል።
  ነገር ግን  እንደ አገራችን  የመሰለች በጥቂት መሪዎች የተያዘ ፖለቲካዊ ስልጣን ያላት አገር የብዙዎችን ዜጎች ጥቅም  በማስቀረት፣ ለብቻው በሚጠቅም አካሄድ በመከተል  ነፃነቱና  መብቱ አፍኖ፤ የሃገር ልኡላዊነትን  ጥሶ፤ ፍፁም በሆነ አምባገነንነት የሚያስተዳድር ስርአት  ከህዙቡ  ጋር  የጠበቀ  ግኑኝነትና መረዳዳት ሊፈጥር ቀርቶ በተቃራኒው በህዝቦች መካከል  በብሔር ብሔረሰቦች መካከል  አንድነት እንዳይፈጠር  ራሱ እሳት እየጫረ  እድሜው ለማራዘም በጣረ ሞት ይገኛል።
     በዚህ መሰረት በአሁኑ ሰአት በተለያዩ የሀገራችን  አከባባቢዎች  በመነሳት ላይ ያሉ የተጠናከሩ ተቃውሞዎች፤ ህዝብ የስልጣን ባለቤት  ባለመሆኑና፤ መሰረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄዎች በመሆኖቸው ብቻ እነዚህን ለማጥፋት ገዥው የኢህአዴግ ስርአት  በማካሄድ ላይ ያለው የሃይል  እርምጃ  መፍትሄ ሊሆን አይችልም።
    እነዚህ በተለያዩ  መንገዶች   በአፋኙ ገዥው  ሰርአት  የሚነሳ ያለው  ህዝባዊ የማእበል ትግል  በአንድ ግዜ የተከሰተ ሳይሆን ለሩብ ዘመን ያክል የህዝቦች ዴሞክራሲዊ ጥያቄዎችና ፍላጎት ጥቅም ለማረጋገጥ በሚል በግል ይሁን በቡዱን ማመልከቻ እያቀረበና እየተታገለ የሚፈታለት ኣካል አጥቶ ከግዜ ወደ ግዜ  እየተባባሰ  የመጣ ነው።
 በመሆም ደግሞ በስልጣን የሚገኝ ገዥው የኢህአዴግ ስርአት  ህግና ስርአት ተከትሎ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ  በተገላቢጦሽ ሆኖ ይህ   የምንታዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞ  በተለይ ደግሞ  የኦሮሞ ህዝብ ተቃውሞ  ማለት  በገጠር ይሁን በከተማ  የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት በተለይ ደግሞ  የከፍተኛ ተቋም ዩኒቨርስቲዎች  በከፍተኛ  ወኔና ሞራል  ተነስተው  የህግ የበላይነትን ለመረጋገጥና  ስልጣን የህዝብ ይሁን ብለው በሰለማዊ መንገድ ጥያቄ  በሚያቀርቡበት ግዜ  ጥያቂዎቻቸውን በመረዳት ተገባ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ  አስፈላጊ ያልሆነ በሃሶት በመወንጀል  በጥይት በመጨፍጨፍ  የንፁሃን ዜጎች ህይወት በጎዳና  ወድቆ እንዲቀር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
  ይህ በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ትግል ህገ መንግስት  ከሚፈቅደው  ህግ ውጭ ሳይሆን  ዜጎች ባላቸው ዴሞክራሴዊ መብት ተጠቅመው  ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ባሉበት ግዜ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ካድሬዎቻችው   ለፀጥታ ሃይሎች ትእዛዝ  በመስጠት  በሰለማዊ ህዝብ ላይ የሚያወርዱትን ድብደባና እስራት  የገዥው   ስርአትን  የአምባገነንነት ባህሪ መገለጫ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም።
  የገዥው የኢህአዴግ  ስርአት  ያለ አንዳች ህጋዊ አሰራር  በንፁሃን ወጣት ተማሪዎችና  በሌሎች ሰለማዊ ህዝብም ለህይወት ህለፈት  ሲፈርዱባቸው   የብዙ ተማሪዎች ቤተሰብ ከመኖርያ ቤቶቻቸው በማፈናቀል ሲያንገላቱ  እንደዚሁም ደግሞ  የተቃዋሚ ድርጅቶት  አባሎቻቸው  በአይነ ቁራኛ የሚያዩዋቸው  ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች በሌሊት ካሉበት እየታፈኑ  በእስር  እንዲገቡ በማደርግ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ አይኑ አፍጥጦ ሊውጣቸው  በዝግጀት ላይ ያለው  የህዝብ  ቁጣ ሰብብ ፈጥሮ ለመቀልበስ የውስጣዊ  ችግሮቻችው  ለውጭ ሃይሎች  በስም ማጥቆር ላይ ተሰማርቶ ይገኛሉ። 
 የህዝቦችን ህገ መንግስታዊ መብትና  ጥያቄ  አፍነው ፍፁማዊ በሆነ  አገዛዝ  ለመቀጠል ዛሬም ካለፉት ስርአታት በባሰ መልኩ   አደባባይ ለወጡ  ሰለማውያን  ታጋዮች  በብረት ሃይል  ኣንገታቸው እንዲደፉ ሙከራ ላይ ቢሆኑም  ህዝቡ  በበለጠ   እንዲነሳሳ አስችሎታል።
  ሰለሆነም የህዝቦች አፈናና ጥያቄዎች የወለደው ትግል   ለፍትህ ለእኩልነትና  ለዴሞክራሲ  ለወጥ  በመካሄድ ላይ ያለወን  ህዝባዊ  ቁጣ  በብረት ሃይል  በማፈን ፍፁም ሊገታ አይቻልም!!!


No comments:

Post a Comment