Monday, March 21, 2016

በሁከትና በግርግር የሚፋጠን ልማት ውጤቱ ውድቀት ነው!!



  በሁከትና ግርግር የሚፋጠን የአንድ አገር መሰረተ  ልማት በእያንዳንዱ ዜጋ አንፃር ሲለካ እድገትና ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ብለህ መጠበቁ ውጤቱ ከውድቀት ያለፈ ሌላ ትርጉም ሊያመጣ አይችልም።

 ምክንያቱም በተግባር በታሪክ  እንደታየው የአንዲት አገር ገዢው ስርአት በግርግር ውስጥ ሆኖ የሚያካሂዳቸው መሰረተ ልማት የጦርነትና የጥፋት ኢኮኖሚ ሲገነባ በዴሞክራሲ ሂደት የህዝብ ውክልና ያለው ገዢው ስርአት ደግሞ ለህዝብ በሚያሳትፍና ግልፅነት በተሞላበት አኳሃን መግባባት ፈጥሮ ለአገርና ለህዝብ የሚረባ ስራ ያፋጥናል ብቻ ሳይሆን ለሌላው እና ለመጪው ትውልድ ከግጭት የሚያድን በጥናት እና እቅድ የሚመራ ቀጣይነት ያለው  ህዝባዊ ልማት ይከተላል።

   በሁከትና ግርግር ፖሊሲ እየተከተሉ በሀገርና በህዝብ ሃብት የሚንደላቀቅ የኢህአዴግ ፀረ ህዝብ ስርአት  የመሰረተ ልማትና እድገት ተረት ተረት በውሸት ሪፖርት ተሸፍኖ አደባባይ ወጥቶ ያለው እፍረት እየተገለፀ መጥተዋል፣ አሁንም ይህ ሰራው በመቀጠል ላይ ይገኛል ብቻ ሳይሆን ለቀጣይም ቢሆን ለ40ና 50 አመታት ያህል የህዝብ ስልጣን በሃይል ተቆጣጥሮ የአገሪቱን ሃብት ያለ ተጠያቂነት ለመኖር እየዘረፈ በመደናገር ስራ ተጠምዶ ይገኛል።

    ባላፉት 25 አመታት ውስጥ ይሁን በአሁኑ ጊዜ በሰፊው መሬታችን ላይ በተለያዩ የአገራችን ሃብቶች ምንጩ በማይታወቅ መልኩ ሃብት የሚያካብቱበት የሙስና መርብ ተፈጠሮው በመሰረተ ልማትና በተቋማት  ስም እየተባለ በሃይል ከንፁሃን ዜጎቻችን እጅ እየዘረፉ ካለ በቂ ካሳ ወደ አልመረጡት ቦታ በመውሰድ ሲያንገላቷቸው እንደቆዩ  የሚጠፋው  ማንኛውም ወገን የለም።

    ይህ በየቀኑ በህልማቸው  አሰመዘገብነው የሚለው እድገት ሲታይ ከድሃ ህዝብ በግብር እና በሌላ መንገድ እየወሰደ ከአቅም በላይ የዉጭ ብድር ተከፍሎ የተወሰኑ ፕሮጀክቶች ጀምሮ ለግንባታው የበጀተው ገንዘብ በሙስና ተመልሶ በመበላቱ ፕሮጀክቶቹ በህዝብ ልማት ሳይዉል ገና እያለ ለፖለቲካዊ ጥቅም ስራ ሲያዉሏቸው ይታያል፣ ከዚህ አልፎ ደግሞ ለጦር መሳርያና ለፀጥታ እንዲሁም በስለያ  አካላት እጅ  ከመዋል አልፎ በኢኮኖሚ ግንባታ ስራ ሲያዉሉት ባለመታየቱ የተነሳ በአሁኑ ጊዜ በአገራችን በድርቅ አደጋ ምክንያት ከ18 ሚልዮን ህዝብ በላይ   በቂ እርዳታ እጥቶ በረሃብ አለንጋ እየተቀጣ ያለው ጭቁኑን ህዝብ ሊያድነው በቻለ ነበር።

     ምክንያቱ በመሬትም ቢሆን እስከ አሁን ድረስ ያረጋገጠውና የሚታይ  የሚጨበጥ ኢኮኖሚያዊ እድገት የለም። በእርግጥ በሚገለፅ የነበረው ሽፋን ለይስሙላ የሚፋጠን የመሰረተ ልማት ግልፅ የሆነ ፖሊሲና ጥናት የሌለው ለይስሙላ የውጣ  በመሆኑ የቡዙዎቹን ጥቅም እረግጦ ከዉስጥ ኩባንያዎችና የግል ባለሃብቶች በመቀናጀት በህዝባችን ህይወት ላይ ቁማር እየተጫወተ የሚገኝ ቡድን መሆኑ ሁሉም ዜጋ የሚያዉቀው ሃቅ ነው።

  በዚህ መሰረት የዚህ ተግባር ቅጥያ ደግሞ በዚህ ሳምንት ዉስጥ በደቡብ ክልል ነዋሪዎች ላይ ኦሞ አከባቢ የሚገኙ የተለያዩ ብሔረሰቦዎች የሚኖርበትን ቦታ ለሽኮር ፋብሪካ ልማት ተፈልጒል በሚል ምክንያት ከመኖርያ ቤታቸው በፀጥታ ሃይሎች ኢ - ሰብአዊ በሆነ መንገድ በግፍ ታስረው ወደ አልፈለጉበት  በረሃማ ቦታዎች ሲጥሏቸው ታይተዋል፣

   ይህ ደግሞ ለህዝብ እድገትና ጥቅም ታስቦ ሳይሆን ገዢው ስርአት ለግላዊ ጥቅሙ ሲል የሚያድርገው የማጭበርበ ፖለቲካል-ኢኮኖሚ እንጂ ለህዝብ እድገት ብሎ የሚያፋጥነው የህዝባዊ ልማት አካል አይደለም።ምክንያቱም የኢህአዴግ መሪዎች በስልጣን ጥማት ምክንያት አይናቸው የታወሩ በመሆናቸው። የስልጣን የእድሜቻው ዋስትና የሚሆናቸው የራሳቸው መላ  ህዝብ ከህዝብ አጋጭተህ ግርግርና ብጥብጥ በመፍጠር ከሚል ፈሊጥ ዉጭ መቀጠል የማይችል ስርአት መሆኑን በደምብ አድርጎ ያዉቃል።ሰለዚህ በግርግር እና በብጥብጥ የሚፋጠን ልማት ዉጤቱ ሲለካ ዉድቀት እና ኋላቀርነት በመሆኑ ሁሉም ወገን በአንድነት በመሆን ተሳስታችኃል ሊላቸው ይገባል።

No comments:

Post a Comment