Friday, April 15, 2016

የኦሆድዴ ደርጅት ባለፈው ሳምንት የተመሰረተበትን 26 አመት በምእራብ ወለጋ መንዲ ከተማ እያስከበረበ በነበረበት ግዜ በነዋሪ ህዝብ ተቃውሞ እንዳጋጠመው ታውቀ።



በደረሰን መረጃ መሰረት፣ ተቃውሞ እያሰሙ  በነበሩ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ላይ የሰረአቱ ፖሊሶችና ወታደሮች በከባድ ደብድበው ለጊዜው እንደበተኗቸው የገለፀው መረጃው፣ ቢሆኖም ግን የገዢው ሰርአት ታጣቂዎች ከስፈራው እንደሂዱ የህዝቡ ተቃውሞ በከባድ መልኩ ተጠናክሮ ሰልፋቸው በቀጠሉበት ግዜ፣ ኦሆድዴድ የኦሮሞን ህዝብ አይውክልም፤ የህዝብ ጥያቂ እስከልተመለሰ ደረሰ ተቃውሞ ይቀጥላል፤ በአፈና የሚፈታ የለም፤ ዛሬም ይሁን ነገ ለሰብአዊና ለዴሞክራሲ መብታችን እንታገላለን፤ ወዘተ የሚሉ መፈክሮዎችን በማጉላት የተቃውሞ ደምፃቸውን እንዳሰሙ ለማውቅ ተችሏል፣፣

 የገዢው ሰርአት ፖሊሶች እየተካሄደ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ሰለተደናገጡ በከተማው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ህዝቦችን በደቂቅ በመከታተልና ከሁለት በላይ ሆኖ በአንድ ለሚጎዙ ተማሪዎች ሳይቀር ለምን ተሰብስባችሁ ትሂዳላችሁ እያሉ በዱላ በመቀጥቀጥ በመበተን ተጠምደው እንደነበሩ ከቦታው የአይን ምስክሮች ዋቢ በማደረግ መረጃ ጨምሮ አስረድቷዋል፣፣

No comments:

Post a Comment