Saturday, April 2, 2016

በመቐለ ከተማ በተደጋጋሚ ጊዜ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ እያጋጠመ እንዳለ ምንጮችቻን ከከተማዋ ገለፁ።



እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት፣ በመቐለ ከተማ ቀደም ሲል በትራንስፎርመር እጥረት ምክንያት የወለደው የመብራት ሃይል መቆራረጥ ሲጋጥም እንደነበረ ከገለፀ በኋላ፣ በተለይ ደግሞ ከመጋቢት 9 /2008 ዓ/ም ጀምሮ በአብዛኛው የከተማዋ ወረዳዎች የሃይል መቆራረጥ እያጋጠመ እንዳለ የገለፀው መረጃው፣ በውጤቱም በብረታ ብረት ስራ፤ በድርጅቶች፤ የእንጨት ስራ፤ ዳቦ ቤቶች፤ ባለ ሆቴሎች፤ ኢንተርኔት ካፌ፤ ቁርስ ቤቶችና ሌሎች ድርጅቶች በችግሩ ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራ እየተጋለጡ በመሆናቸው የተነሳ በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ተቸግረው እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
      መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው፣ የከተማዋ ባለ ሃብቶች በመሰብሰብ ሁኔታውን ለማስረዳት ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ፅህፈት ቤት በመሄድ ቢጠይቁም፣ የትራንስፎርመር ማቀያየር እያደረግን ሰለሆንን በቅርብ ግዜ መፍትሄ ይገኛል በሚል የማይተገበር የተለመደ ቃል ቢገቡም፣ ነገር ግን እስከ አሁን ደረስ የታየ ለውጥ እንደሌለ መረጃው አክሎ ገልጿል።




No comments:

Post a Comment